Amhara Youth Association

የማህበሩ አመሰራረት

 
 
                 የአማራ ወጣቶች  ማህበር  አመሰራረት

የአማራ ወጣቶች ማህበር ለማናቸውም የፖለቲካም ሆነ የሀይማኖት ተቋማትና ድርጅቶች የማይወግን ፤ ነፃ ማህበር ሆኖ በሚመለከታቸዉ አካላት እዉቅናና ፈቃድ በአዋጅ ቁጥር 194 መሰረት ፤ የወጣቶችን ሁለንተናዊ ተሳትፎና ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ እንዲሁም ንቁ ተሳታፊ እንዲሆኑ ለማስቻል በ1995 ዓ.ም የተመሠረተ ማህበር ነው።

የዞን ቅርንጫፎች

አዳዲስ ዜናዎች

“የተደራጁ ወጣቶች የሰላምና የልማት አቅም ናቸው”

“የተደራጁ ወጣቶች የሰላምና የልማት አቅም ናቸው” የአማራ ወጣቶች ማህበር 6ኛ መደበኛ ጉባዔ ጳጉሜ 01/ 2017...

የተደራጁ ወጣቶች የሰላምና ልማት አቅም ናቸው።

የተደራጁ ወጣቶች የሰላምና ልማት አቅም ናቸው። በሚል መሪ ሃሳብ የአማራ ወጣቶች ማህበር 6ኛ መደበኛ ጠቅላላ...

“የማኅበሩ ዓላማ የወጣቶችን ተጠቃሚነት ማረጋገጥ ነው”

“የማኅበሩ ዓላማ የወጣቶችን ተጠቃሚነት ማረጋገጥ ነው” የአማራ ወጣቶች ማኅበር ”የተደራጁ ወጣቶች የሰላም እና የልማት አቅም...

በክረምት የበጎ ፍቃድ አገልግሎት ከ53 ሚሊዮን በላይ የሚሆኑ የህበረተሰብ ክፍሎችን

በክረምት የበጎ ፍቃድ አገልግሎት ከ53 ሚሊዮን በላይ የሚሆኑ የህበረተሰብ ክፍሎችን ተጠቃሚ ማድረግ ተችሏል- ኤርጎጌ ተስፋዬ...

የማህበሩ ፕሮግራም

ስለ ህገ-ወጥ ስደት ግንዛቤ መስጠት

ህገወጥ የሰወች ዝውውር የሚያስከትለውን ጉዳት በተመለከተ ለ10000 ሽህ ያህል ወጣቶች ግንዛቤ መፍጠር፣ወጣቱ በሃገሩ ሰርቶ መለወጥ እንደሚችል ትምህርት መስጠት።

ለወጣቶች የስራ እድል መፍጠር እና በኢኮኖሚ ማጎልበት

በግብርና እና በከትሞች በሚካሄዱ ልማታዊ እንቅስቃሴዎች ላይ የወጣቶችን ተሳትፎና ተጠቃሚነት ማረጋገጥ፤ በተፈጥሮ ሀብት ልማት ስራ ሁሉንም የማህበሩ አባላት በተደራጀ መንገድ ተሳታፊ ማድረግ፤በተፈጥሮ ሀብት ስራ የዳኑ እና ያገገሙ ተራሮችን መጠበቅና መንከባከብ ላይ የማህበሩ አባላት የስራ እድል ተጠቃሚ እንዲሆን ማስቻል።በገጠር የእርሻ መሬት ለሌላቸዉ ወጣቶች ከሚመለከትዉ አካል ጋር በመነጋገር መሬት የሚያገኙበትን ሁኔታ ማመቻቸትና 20,000 የማህበሩን አባላት በመስኖ ስራ እንዲሰማሩ ማድረግ። ከቴክኒክና ሙያ ኢንተርኘራይዞች ልማት ጋርና ሌሎች አጋር አካላት ጋር በመነጋገር 15,000 ለሚሆኑ የከተማ የማህበሩ አባላት የስራ እድል መፍጠር፣ በማህበር ተደራጅተው ስራ በመሰራት ላይ የሚገኙ አባላትን መደገፍ፣ የብድር የመሰሪያ ቦታ ጥያቄወች ያለምንም ቢሮክራሲ ምላሽ የሚያገኙበትን መንገድ ማመቻቸት።

በፖለቲካና መልካም አስተዳደር ዘርፍ ንቁ ተሳታፊ ማድረግ


በየደረጃው ባሉ መዋቅራችን የፀረ-ሙስናና ስነ-ምግባር ክበባትን ማቋቋም! በብልሹ አሰራር እና የመልካም አስተዳደር ችግሮች ዙሪያ ለማህበሩ አባላት እና ለዞንና ለወረዳ አመራሮች የክልል አጋር አካላትን በማስተባበር ስለፀረ ሙስናና ብልሹ አሰራር ትግል የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና መስጠት።ከዚህ በተጨማሪም ከየትኛውም ፖለቲካ ፖርቲ ነፃ የሆነ አደረጃጀት በመፍጠር በቀጣይ 2018 ዓ.ም የሚካሄደዉን 7ኛዉ ሀገራዊ ምርጫ በክልላችን በሁሉም አካባቢዎችና በአዲስ አበባ

በትምህርት ጤና እና ስነዋልዶ ለወጣቶች ግንዛቤ መስጠትና ተጠቃሚ እንዲሆኑ ማድረግ፤


ስለ አደገኛ መድሀኒቶች እና እፆች ጐጅነት እንዲሁም ይህን ተከትለው ስለሚመጡ እንደ ኤች አይ ቪ እና መሰል የጤና ቺግሮች ለአባላት እና 500,000 ለሚሆኑ ወጣቶች ግንዛቤ መፍጠር፤ከሚመለከታቸዉ አካላት ጋር በመተባበር ወጣቶች ነጻ የትምህርት እድል እንዲአገኙ ማስቻል፤የወጣት ማዐከላት እንዲገነቡ፡ከዚህ በፊት የተገነቡትንም ማጠናከር እና ተገቢውን አገልግሎት እንዲሰጡ ማስቻል።

አጋሮቻችን

ያግኙን

Name
Scroll to Top